Jump to Navigation

The Undergoing Hospital Expansion Projects In The City To Complete This Year

Published on: Mon, 2013-12-23 00:00
Black Lion hospital image

በአዲስ አበባ ከተማ በ450 ሚሊዮን በሚጠጋ ወጪ በአምስት ሆስፒታሎች እየተካሄደ ያለው የማስፋፊያ ሥራ በዘንድሮ በጀት ዓመት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የከተማው የኮንስትራክሸንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቁ አሁን ያለውን የጤና ሽፋን 100 በመቶ ያደርሰዋል።

የከተማው የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ከበደ እንደተናገሩት የሆስፒታሎቹ የግንባታ ደረጃ በአማካኝ ከ89 በመቶ በላይ ደርሷል።

በየካቲት፣ በዳግማይ ሚኒሊክ፣ በጋንዲ፣ በዘውዲቱና በራስ ደስታ ሆስፒታሎች እየተከናወነ ያለው ይህው የማሰፋፊያ ፕሮጀክት ከአራት እስከ ሰባት ፎቅ ከፍታ ያላቸው ናቸው።

እነዚህ ግንባታዎች አሁን ያለውን የጤና አገልግሎት ለማሳደግ ታሳቢ በማድረግ እየተገነቡ ሲሆኑ በአሁን ወቅት 86 በመቶ የደረሰውን የከተማውን የጤና ሽፋን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 100 በመቶ ያደርሰዋል።

አካል ጉዳተኞችን ያማካለ የግንባታ ሂደት የእናቶችና የህጻናት ሞት በመቀነስ አገሪቱ እያስመዘገበች ያለችውን ውጤት እሚያግዝ ታምኖበታል፡፡

የሆስፒታሎቹ ወጪ ሙሉ በመሉ በመንግስት የተሸፈ ሲሆን በአጠቃላይ በከተማው ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር  የሆስፒታሎች ማስፋፊያና የጤና ጣቢያዎች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑንም ለኢዜአ ተናግረዋል።

Source: Ethiopian Radio and Television Agency (ERTA)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C