Jump to Navigation

Three New Airports Start To Give Service From Next Mont

Published on: Sat, 2013-12-07 00:00
Image showing logo of the Ethiopian Airports Enterprise

ኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በመጪው ታህሳስ ወር ሶስት ኤርፖርቶችን ስራ ሊያስጀምር ነው።

ወደ ስራ ይገባሉ ተብለው ከሚጠበቁት መካከል ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የሰመራ ኤርፖርት አንዱ ነው።

የድርጅቱ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድም ተክሉ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ፥ ይህ ኤርፖርት በታህሳስ ወር የመጀመሪያ ቀናት ላይ ስራ ይጀምራል።

ኤርፖርቱ ሰባ መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው ጊዜያዊ ተርሚናል ያካተተ ፥ አንድ Q400 አውሮፕላን የሚያሳርፍ የማረፊያ ሜዳም ተገንብቶለታል።

በቀጣይም ኤርፖርቱን በ180 ሚሊዮን ብር ለማስፋፋት ድርጅቱ ጨረታ ያወጣ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አሸናፊውን በመለየት ሂደት ላይ ይገኛል ነው ያሉት አቶ ወንድም።

ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የአሶሳ ህዳሴና ከ298 ሚለዮን በር በላይ የወሰደው የጅማ አባጅፋር ኤርፖርቶችም በታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ ስራቸውን በይፋ እንደሚጀምሩ ሃላፊው ተናግረዋል።
Source: Fana Broadcasting Corporate(FBC)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C