Out Of 13 City’s Under Construction Bridges, Squares Three Go Operational
በ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጭ በአዲስ አበባ ከተማ በመገንባት ላይ ከሚገኙ 13 ድልድዮች እና አደባባዮች ሶሰቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቁ።
ከሚገነቡት መካከል መገናኛ ፣ 22 ጎላጉል ህንጻ አካባቢ ፣ ኡራኤል ፣ ሜክሲኮና ልደታ አካባቢ አደባባዮች ሲሆኑ ፤ ማዕድን ሚኒስቴር ፣ ለም ሆቴል እና ቄራ አካባቢ ደግሞ ተሻጋሪ ድልድዮች ናቸው።
ሜክሲኮ እና ልደታ አካባቢ የተገነቡት ድልድዮች ግንባታ መጠናቀቁንም ነው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ያስታወቀው። የድልድዮቹ ግንባታ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ነው የተጠናቀቀው።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ፈቃዱ ሃይሌ እንደተናገሩት ፥ ድልድዮቹ በጥር ወር ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ሲሆኑ የቀሪዎቹ ግንባታም እስከ የካቲት ወር ድረስ ይጠናቀቃል ።
የመገናኛ ፣ ጎላጉል አካባቢ ፣ኡራኤል አደባባይ እና የቄራ ተሻጋሪ ድልድይ ግንባታ በአሁኑ ሰአት የአንድ ወገን ግንባታቸው እየተገባደደ ነው።
ግንባታቸው የተጠናቀቀውና በመገንባት ላይ ያሉት አደባባዮች እና ድልድዮች የባቡር ሃዲዱንና እና የመኪና መንገዱን የመለየት ሚና ይኖራቸዋል።
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባለፈው አመት ሚያዚያ ወር ላይ ከቻይና ሲ አር ቢ ሲ እና ከሃገር በቀሉ ትድሃር ኩባንያዎች ጋር ውል ተፈራርሞ ወደስራ መግባቱ ይታወሳል።
Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)
- 2093 reads