New Construction Industry Policy Drawn Up
የግንባታ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚገጥሙትን ውስብስብ ችግሮች መፍታት የሚረዳ አዲስ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ተረቀቀ።
የከተማ ልማት ፣ የኮንስትራክሽንና ቤቶች ግንባታ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ኃይለሚካኤል ተፈራ እንደተናገሩት ፥ መንግሥት የዘርፉን ተግዳሮቶች ለማስወገድ የተለያዩ እርምጃዎች ሲወስድ ቆይቷል።
በኢንዱስትሪው ከሚታዩት ችግሮች መካከል ዋነኛው የግንባታ ፕሮጀክቶችን በታለመለት ጊዜና ወጪ በአግባቡ አለመፈጸም አንዱ መሆኑን ጠቁመው ፥ የግንባታው ዘርፍ ሥርዓት ባለው መንገድ እንዲመራ አዲስ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ መዘጋጀቱን አመልክተዋል።
ፖሊሲው የግንባታው ኢንዱስትሪ ተስማሚ ቴክኖሎጂ እንዲጠቀምና የአገሪቱን የግንባታ ዘርፍ አቅም እንዲገነባ የሚያደርግ ከመሆኑ ባሻገር የፈጠራ ሥራን የሚያበረታታ ፣ ስነ-ምግባራዊ የሥራ አፈፃጸም እንዲሰፍን የሚያደርግ መሆኑን አብራረተዋል።
በተጨማሪም ፖሊሲው የሥራ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሥርዓት እንዲኖር ከማስቻሉም በላይ ኢንዱስትሪው የግንባታ ሕግና ሥርዓት ተከትሎ እንዲጓዝ የሚያስችል መሆኑን የዘገበው ኢዜአ ነው።
Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)
- 948 reads