Ministry Announces To Curb Infrastructure Problems That Hinder Investors
ግል ባለሃብቶች በሃገሪቱ ልማት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ የደርጋል አሉ ሚኒስትሩ።
ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ የገላን ከተማ አስተዳደርና የከተማዋ ባለሃብቶ የ2006 የጋራ ዕቅድ ምክክርን በከፈቱበት ወቅት ነው ይህን ያሉት።
ለሃገሪቱ የኢንዱስትሪ ሽግግር ዕቅድ ስኬታማነት ጉልህ ሚና ያላቸው የግል ባለሃብቶች እንቅፋት የሆኑባቸው የኤሌክትሪክና የውሃ እንዲሁም ሌሎች የመሰረተ ልማት አቅርቦት ችግር አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።
በቅርቡ የተመሰረተችው የገላን ከተማ 266 የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በ13 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ካፒታል በተለያዩ የልማት ስራዎች ለመሰማራት ማቀዳቸውንና ፤
73 ፕሮጀክቶችም ግንባታቸውን ጨርሰው ወደስራ ለመግባት የኤሌክትሪክ ሃይል በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን የገላን ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉጌታ ከበደ ተናግረዋል።
Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)
- 624 reads