Jump to Navigation

Ministry: 72.24 mln USD Gained From Mining Sector

Published on: Sun, 2013-10-27 00:00
image showing potash

በሩብ የበጀት ዓመቱ የተለያዩ ማዕድናትን ወደ ውጪ በመላክ 72 ነጥብ 24 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ረዳት ኃላፊ አቶ ጫላ ቦንሳ እንደገለፁት፤ የተገኘው ገቢ በኩባንያዎችና ባህላዊ የማዕድን አምራቾች አማካኝነት 3 ሺ 167 ነጥብ 40 ኪሎ ግራም ወርቅ፣ የተለያዩ የጌጣጌጥ ማዕድን፣ ፕላቲኒየም እና 102 ነጥብ 97 ቶን ታንታለምና እምነበረድ ወደ ውጪ በመላክ ነው።
ረዳት ኃላፊ አቶ ጫላ ቦንሳ ከተገኘው ገቢ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው ወርቅ መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህም 1 ሺ 890 ኪሎ ግራም ወርቅ ከትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ከደቡብና ከጋምቤላ ክልሎች ያሉ ባህላዊ ወርቅ አምራቾች የተመረተ ሲሆን፤ በኩባንያዎች ደግሞ 605 ኪሎ ግራም ወርቅ፣ 90 ነጥብ 5 ሜትር ኩብ እምነ በረድና 40 ኪሎ ግራም ፕላቲኒየም ተመርቶ ለውጪ ገበያ መቅረቡን ገልፀዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሩብ የበጀት አመቱ ከልዩ ልዩ የማዕድን ፍቃድና ተያያዠ አገልግሎቶች 43 ነጥብ 96 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 33 ነጥብ 47 ሚሊዮን ብር ገቢ እንደተገኘ የጠቆሙት አቶ ጫላገ ቢውን በቀጣይ ወራት ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
እንደአቶጫላገለፃበሩብየበጀትዓመቱ 12 ነጥብ9 ቢሊዮን ብር ላስመዘገቡ ኩባንያዎች ፍቃድ የተሰጠ ሲሆን፤ ከኩባንያዎቹ መካከል በፖታሽ ማዕድን ላይ በአፋር የተሠማራው የካናዳው አላና ፖታሽ ኩባንያ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።
የማዕድን ሚኒስቴር በተለያዩ ኩባንያዎችና ባህላዊ የማዕድን አምራቾችን በመጠቀም ወርቅ፣ ዕምነ- በረድ፣ ፕላቲኒየም፣ ታንታለምና የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናትን ወደ ወጪ በመላክ የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሪ ለማሳደግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዋልታዘግቧል።
Source: Ethiopian Radio and Television Agency (ERTA)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C