Mesobo cement factory will begin manufacturing suitable cement for environment
መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ ሲሚንቶ ማምረት ሊጀምር ነው
መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ ወጪ ለመቀነስ የሚያስችልና ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ ሲሚንቶ ማምረት ሊጀምር ነው፡፡
ፖርትላንድ ላይምስቶን የተባለው ይህ ምርት በአገራችን አዲስ የሆነና ፥ ለግንባታው ዘርፍ የሚወጣውን ወጪ በመቀነስ ረገድ የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡ከሲሚንቶው ጋር ላይምስቶን ከ6 እስከ 35 በመቶ ድረስ የሚቀላቀል ሲሆን ፥ ይህም የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ መጠንን ስለሚቀንስ አካባቢው እንዳይበከል ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
በአገልግሎት ላይ ሲውልም የሚደባለቀው የውሀ መጠን አነስተኛ ስለሚሆን ቶሎ መጣበቅ ይችላል ነው የተባለው፡፡
ምርቱ ከተመረተ በኋላም በፋብሪካ መሸጫ ዋጋው የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በ130 ብር መቅረብ ይጀምራል መባሉን ትዕግስት መንግስቱ ዘግባለች፡፡
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 19 ፣ 2005
Source:-Fana broadcsting corport
- 1427 reads