Jump to Navigation

Meles Zenawi Memorial Referral Hospital Inaugurated In Jigjiga

Published on: Sun, 2013-12-08 00:00
Image of Meles Zenawi Memorial Referral Hospital in Jijiga

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የተገነባው የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ሪፈራል ሆስፒታል ተመረቀ።

ሆስፒታሉ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በይፋ ተመርቋል፡፡

ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሆስፒታሉ ከ5 ሚሊየን ለሚልቁ የክልሉና አጎራባች አገራት ዜጎች የህክምና አገልግሎት የመስጠት አቅም አለው።

የሆስፒታሉ መገንባት የክልሉ ዜጎች ወደ አዲስ አበባ እና የውጭ ሃገራት የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያደርጉትን ጉዞና ዕንግልት እንዲሁም አቅም የሌላቸው የክልሉ ነዋሪዎች በህክምና እጦት ምክንያት የሚደርስባቸውን የጤና ቀውስ ያስቀራል ተብሏል።

ባለ ሁለት ህንፃው የመለስ መታሰቢያ ሪፈራል ሆስፒታሉ ከህንፃው አናት ላይ 3 ሄሊኮፕተሮችን ማሳረፍ የሚያስችል ቦታም ተዘጋጅቶለታል።

ከዚህም በተጨማሪ በህንፃው ውስጥ ለአካል ጉዳተኞችና ህሙማን በጋራ የሚጠቀሙበት መንገድና 19 ሰዎችን በአንዴ መጫን የሚችሉ 4 አሳንሱሮች ተገጥመዋል።

ህሙማን ተኝተው የሚታከሙበት 700 አልጋዎችን የያዘ ሲሆን፥ በአንዴ 500 ሰዎች ተኝተው መታከም የሚችሉበትም ነው።

ወደ ሆስፒታሉ የሚገባን አቧራና ከሆስፒታሉ የሚወጣውን ሽታ መምጠጥና በንፁህ አየር መሙላት የሚያስችል ዘመናዊ መሳሪያም ተገጥሞለታል።

በሆስፒታሉ ድንገት የኤሌክትሪክ መቋረጥ ቢያጋጥም ለ7 ሰዓት የኤሌክትሪክ ሃይልን ይዞ መቆየት የሚችል መሳሪያም መገጠሙን የሚናገሩት አቶ እድሪስ፥ የንፁህ ውሃ ፍላጎቱንም በግቢው ውስጥ ከተቆፈረ ጉድጓድ በሚወጣው ውሃ ሙሉ በሙሉ መጠቀም የሚያስችለው ስራም ተሰርቷል ።

የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ሪፈራል ሆስፒታል 3 ዓመት ተኩል የግንባታ ጊዜን ወስዷል።
Source: Fana Broadcasating Corporate(FBC)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C