Jump to Navigation

Injibara-Ayman Road Construction Commences With 3.3 bln Birr Budget

Published on: Tue, 2013-08-27 00:00
Image showing a rural asphalt road

ከእንጅባራ-ቻግኒ- ፓዌ-ፈንድቃ-አይማን ከ3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀመረ ።
ከ 175 ኬሎሜትር በላይ የሚረዝመው መንገዱ በገጠር እስከ 10 ሜትር ፥ በከተማ ደግሞ እስከ 14 ሜትር ስፋት ያለው ነው።
ፕሮጀክቱ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመት ከስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ተናግረዋል።
ለመንገዶቹ ግንባታ የሚውለው በጀት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ሲሆን ፥ መንገዶቹ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ በሚገኘው የህዳሴው ግድብና በጣና በለስ የተቀናጀ ስኳር ፕሮጀክቶች የሚያስኬዱ መስመሮችን አቋርጠው ያልፋሉ ፡፡
ይህም የፕሮጀክቶቹን እንቅስቃሴ ከማፋጠን ባሻገር የአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን ግንኙነት በማጠናከር ፥ የክልሎቹን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንደሚያፋጥነው ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት።
Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C