Jump to Navigation

Half Of The Money Collected For The Ethiopian Great Renaissance Dam So Far

Published on: Thu, 2014-01-16 00:00
Grand Ethiopian Renaissance dam project image

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በህዝቡ የማይተካ ድጋፍና ቁርጠኝነት በተፋጠነ ሁኔታ እየተገነባ ነው አለ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ብሄራዊ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝባዊ ንቅናቄ  መድረክ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

በውይይቱ  የታላቁ ህዳሴ ግንባታ ብሔራዊ ማስተባበርያ ፅህፈት ቤት ፤ ላለፉት ሁለት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ቃል ከተገባው 10 ቢሊየን ብር መካከል ከግማሽ በላይ መሰብሰቡን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የታላቁ ህዳሴ ግንባታ ማስተባበርያ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዮናስ አስናቀ በበኩላቸው ፥ ከመንግስት ሰራተኛው ፣ ዝቅተኛ ገቢ ካለው የንግዱ ማህበረሰብና ከነዋሪው ከ335 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

በያዝነው አመትም 250 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን ፥ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል።

በተያያዘ ዜና በአሁኑ ወቅት ለዋናው ግድብ መገንቢያ የሚሆነው ቦታ ተመርጦ ለግንባታው የሚያገለግሉ ከ2000 በላይ መሳሪያዎች ተገዝተው ወደ ስራ ተገብቷል።

ግድቡ በአሁኑ ወቅት 30 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ፥ በመጪው አመት አጋማሽ 750 ሜጋ ዋት የኤሌከትሪክ ሃይል ማመንጨት ይጀምራል።

ግድቡ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር አሁን ያለውን 41 በመቶ የኤሌክትሪክ ስርጭት ሽፋን ወደ 75 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከሌሎች ግድቦች ከሚመነጨው ሀይል ጋር በመጣመርም ሀገሪቱ በ2008 የምትፈልገውን 10000 ሜጋ ዋት እንደሚያሟላ ተገልጿል።

ከሀገራዊ ፋይዳው በተጨማሪ ግድቡ በዓመት 1.5 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል ተብሎ ይገመታል።

Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C