Jump to Navigation

Gilgel Gibe III Hydropower Project 77 Percent Completes

Published on: Thu, 2013-10-10 00:00
image of Gilgel Gibe Hydro power project

ግልገል ግቤ 3 የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት 77 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ፥ ግድቡ በተያዘለት የግዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው ተባለ ።

በአሁኑ ወቅት በፕሮጀክቱ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ከ6000 በላይ ሰራተኞች ሲኖሩ ፥ ከነዚህ ውስጥ 80 በመቶዎቹ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውም ተመልክቷል።

ስራው በሁለት ፈረቃዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ እና ከጥቂት የማጠናቀቂያ ስራዎች በስተቀር አብዛኛው የግድቡ ስራዎች መጠናቀቃቸውም ነው የተገለፀው።

ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቀቅ 1870 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት በአገሪቱ ያለውን የሀይል አቅርቦት እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።
Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C