Jump to Navigation

The First 250 Train Drivers To Be Trained In China

Published on: Tue, 2013-12-03 00:00
Image showing train

ላለፉት 5 ዓመታት በባቡር መሥመር ፕሮጀክት ዝግጅትና ስራ ላይ ላይ የቆየው የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቱን በኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች እንዲካሄድ ለማስቻል በአቅም ግንባታ በኩል ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን የትራንስፖርት ሚንስቴር ገልጿል፡፡

የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በስራ ፈጠራ፣ በአቅም ግንባታና በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ የተገኙ ተሞክሮዎችና ልምዶች ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲ አበባ ውይይት አድርጓል፡፡

ሚንስትር ድአታው አቶ ጌታቸው መንግስቴ በመድረኩ ላይ በባቡር ዘርፍ ያሉ የአቅም ግንባታ ሂደቶችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቶ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስና ምርጥ ተሞክሮዎችን ልምድ ለመለዋወጥ የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ኢንጅነር ጌታቸው በበኩላቸው 45 በመቶ በሀገር ውስጥ ባለሞያዎች የሚቀሳቀሰውን የባቡር ፕሮጀክት በእድገትና ትራንስፎርሜሽኑ መባቻ ላይ ሙሉ ለሙ በሀገር ውስጥ ባለሞያዎች እንዲሸፈን ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በሀገራችን ከዚህ ቀደም ባቡርን አስመልክቶ በከፍተኛ የትምህርት ተቋምም ሆነ በቴክኒና ሞያ ደረጃ ስርአተ ትምህርት ያልነበረ በመሆኑ በሞያው ላይ ሰፊ እውቀትና ልምድ ያላቸውን ባለሞያዎች ከሀገር ውስጥ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ይህንን እጥረት ለመሸፈን ኢትዮጵያዊ ዘርፉን ባለሞያ ለማፍራት ወደ ውጭ ሀገር ሄደው እንዲሰለጥኑ በመደረግ ላይ መሆኑን ነው ዶ/ር ኢንጅነር ጌታቸው የገለፁት፡፡

በአሁኑ ወቅትም 30 ኢትዮጵያዊያን ኢንጅነሮች በሩሲያ 27 ኢንጅነሮች ደግሞ በቻይና በባቡር ምህንድስና ዘርፍ እየሰለጠኑ ነው ብለዋል፡፡ በቅርቡም የመጀመሪያዎቹን 250 የባቡር አሽከርካሪዎች ወደ ቻይና ልኮ ለማሰልጠን ኮርፖሬሽኑ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

በአዲስ አበባም 500 የባቡር መሀንድሶች በድህረ ምረቃ መርሀ ግብር በስልጠና ላይ የሚገኙ ሲሆን 200ዎቹም ዘንድሮ ትምህርታቸውን እንደሚያጠናቅቁ ነው የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢንጅነር ጌታቸው በትሩ ያስታወቁት፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን የግልገል ጊቤ 3 የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ተሞክሮ ያቀረቡት የፕሮጀክቱ ሀላፊ ኢንጅነር አዜብ አስናቀ በበኩላቸው የኢዮጵያ ባቡር ፕሮጀክት አዲስ እንደመሆኑ የረጅም ጊዜ ልምድ ካላቸው የኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቶች ብዙ ልምዶችን ማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ሚንስቴር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሏቸው ፕሮጀክቶች ላይ ያጋጠሙዋቸውን ችግሮችና የተገኙ ውጤቶችን የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡
Source: Ethiopian Radio and Television Agency(ERTA)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C