Jump to Navigation

Expansion Project To Commence For Road From Abune Petros Square To Lideta

Published on: Fri, 2014-01-31 00:00
Road construction in Addis image

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ከ 561 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ እስከ ልደታ ያለውን መንገድ ሊያስፋፋ ነው።

ባለስልጣኑ በዚህ በጀት በጉርድ ሾላና በገላን የመንገድ ጥገናና የዲዛይን ስራ ለማከናወንም ዛሬ ከአምስት ሀገር በቀል ተቋራጮች ጋር የውል ስምምነት ፊርማ አካሂዷል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ ፥ ከአትክልት ተራ በአቡነዼጥሮስ -አውቶቡስ ተራ - ልደታ ዳር ማር የሚዘልቀውን የ4 ኪሎ ሜትር መንገድ ለማሰራት አሰር እና እንይ ከተባሉ ሃገር በቀል ተቋራጮች ጋር የስምምነት ውል ፈርመዋል።

የባቡር ፕሮጀክቱን ተከትሎ በ40 ሜትር ስፋት የሚገነባው ይኸው መንገድ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የገላን ቁጥር 3 የሶስት ነጥብ አምስት ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታም በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ነው የተገለፀው።

ከጉርድ ሾላ- ሰሚት- የካ- አያት ያለውን መንገድ  ለመጠገንና ቁጥጥር ለማካሄድም ባለስልጣኑ  ከተቋራጮች ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል።

Source: Fana Broadcasting Corprate (FBC)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C