Jump to Navigation

The Existing Water Pipe from Megenagna to Mexico is Going to be Replaced by a New one

Published on: Thu, 2013-04-04 08:30
Image of Megenagna to Mexico road model.

ከመገናኛ ሜክሲኮ የተዘረጋውን ነባር የውሃ መስመር በአዲስ መስመር እየተተካ ነው

ለአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ፕሮጀክት ግንባታ አመቺነት ሲባል ከመገናኛ - ሜክሲኮ የተዘረጋውን ነባር የውሃ መስመር የማንሳት ስራ በሶስት ወራት ይጠናቀቃል አለ የከተማው ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን።

ከለገዳዲ   ከ40 አመት በፊት በመንገዱ መሃል አቋርጦ የመጣው መሰመር ነው ለባቡር ግንባታው ሲባል እየተነሳ ያለው። ባለስልጣኑ ከቻይናው ሲጂሲ ኦቨር ሲስ ከተባለ ተቋራጭ ጋር ውለታ በመግባት ከመገናኛ ሜክሲኮ ያለውን 9 ኪሎ ሜትር የውሃ መስመር ከ480 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ አስነስቶ በሌላ የሚተካው።

ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ ተቋራጩ ዘግይቶ ስራውን የጀመረ ቢሆንም ፥ ሰሞኑን ከእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ጀምሮ እስከ ለገሃር ድረስ በሁለት ክፍል የታጠረው ስፍራ  የቧንቧ ቀበራ ተጠናቆ ከሳምንት በኋላ አካባቢው ለትራፊክ ክፍት ይሆናል ብሏል ባለስልጣኑ ።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ እሰኪያጅ አቶ ተስፋዓለም ባዩ እንዳሉት ፥ በኮንትራት ውሉ መሰረት ስራው ሰኔ ወይም ሃምሌ መጀመሪያ ላይ ይጠናቀቃል።

አዲሱ የቧንቧ ቀበራ ስራ  ከመገናኛ ሜክሲኮ እንደተጠናቀቀ አሮጌው መስመር ያለምንም ችግር ተነስቶ የውሃ ስርጭቱ በአዲሱ መስመር ይከናወናል ።

Source: - Fana broadcasting Corporate



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C