Ethio Telecom Collects 8 Bln Birr In First Half Of Budget Year
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሳይንስ ፣መገናኛና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስቴርን የ6 ወራት ስራ አፈፃፀም ገምግሟል፡፡
ባለፉት 6 ወራት በተለይ የኢትዮ ቴሌኮም ለመሰብሰብ ካቀደው 9.5 ቢሊዮን ብር ውስጥ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ማሳካቱን የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ድኤታ አቶ ጌታቸው ነጋሽ በሪፖርታቸው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ከተደራሽነትና ጥራት ጋር ተያይዞ የሚታዩ የተለያዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ የማስፋፊያ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ እያደረገ ቢሆንም በአገልግሎቱ ላይ ግን ጥራት ችግር መኖሩን ቋሚ ኮሚቴው አንስቷል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ራቅ ባሉ ክልሎች የጥሪ ማእከላትን ለማስጀመር እየተደረገ ያለውን ጥረትና በገቢ አሰባሰብ ያስገኛቸውን ተግባራት በጥሩ ጎኑ አይቶታል፡፡
ሚንስትር መስሪያ ቤቱ በቀጣይም የህዝብ መረጃ አገልግሎት መስጫ ማእከላትን ማቋቋምን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብሏል፡፡
እንዲሁም የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የ6 ወር የበጀት አፈፃፀም ዝቅተኛ በመሆኑ በቂ ትኩረት ተሰጥት ሊሻሻል ይገባል ብሏል፡፡
Source: Ethiopian Radio and Television Agency (ERTA)
- 2819 reads