Jump to Navigation

Design Of Hawasa Airport Begins

Published on: Thu, 2014-01-09 00:00
Image showing the partial view of hawassa town

የሃዋሳ ከተማ ኤርፖርት ግንባታን ለመጀመር የሚያስችለው የቦታ ርክክብ ተካሂዶ የዲዛይን ስራ ተጀመሯል አለ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ።

የደቡብ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ ፥ በ2005 ዓ.ም ከ631 ሺህ በላይ በሆኑ የውጭና የሀገር ውስጥ ዜጎች ተጎብኝታ 130 ሚልዮን ብር አስገኝታለች።

የክልሉ ባሀልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘሪሁን ዘውዴ ፤ ከተማዋ የአይን ማረፊያ ሳታጣ ወደ እልፍኟ የሚያደርስ አማራጭ የትራንስፖርት መንገድ በማጣት ብቻ ያሰበችውን ያህል ጎብኝ እንዳላገኘች ተናግረዋል።

ብቸኛው የመጓጓዠ ዘዴ ተሽከርካሪ ብቻ መሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች አቅማቸው የቻለውን ፣ ቀልባቸው የወደደውን የመጓጓዥ ዘዴ እንዳይጠቀሙም ምክንያት ሆኗል።

ለዚህም የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት  ቦታ ተረክቦ የኤርፖርቱን ዲዛይን በማሰራት ላይ ነው።

ለዲዛይኑ አንድ ሚሊየን ብር የተመደበ ሲሆን፥  በአራት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል።

ለግንባታው የሚወጣው ወጪና የግንባታው ጊዜም ከዲዛይኑና ጨረታው መጠናቀቅ በኋላ የሚታወቅ ይሆናል ይላሉ የድርጅቱ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድም ተክሉ።

ይህ በሂደት ላይ ያለውና ሀዋሳ አሻግራ የምታማትረው ኤርፖርት ሲጠናቀቅ ፤ መዲናይቱ አጥብቃ የምትሻውን የቱሪስት ፍሰቷን በእጥፍ የማሳደግ ግብ ጥርጊያው ይሰናዳለታል።

Source: Fortune



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C