Jump to Navigation

Construction Of 10/90, 20/80 And 40/60 Condominium Schemes To Commence In Oromia Region

Published on: Wed, 2014-01-08 00:00
Condominium Houses image

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የ10 /90 20/80 እና የ40 /60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት ምዝገባ ሊጀመር ነው።

በኦሮሚያ ክልል ቀድሞ የተገነቡት ከ22 ሺህ በላይ የጋራ መኖርያ ቤቶች 19 ሺህ የሚደርሱ ዜጎችን የቤት ባለቤት አድርጓቸዋል።

17 ከተሞች ላይ የተገነቡት ወደ 3 ሺህ የሚጠጉ ቤቶች ግን ከ80 በመቶ በላይ መጠናቀቅ ባለመቻላቸው ለመንግስት ድርጅቶች እንዲሸጡ ተደርጓል።

የክልሉ ኮንስትራክሽንና የቤቶች ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አወሉ አብዲ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ እየሆነ ያለውን የ10/90 የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ የዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ ነው ብለዋል።

ከአንድ ወር በኋላ የመጀመሪያ የዝግጅት ምእራፉን አጠናቆ ወደ ምዝገባና ግንባታ የሚገባው የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ ፥ ቀድሞ ጥናት በተደረገባቸውና ፍላጎቱ በከፍተኛ ደረጃ በታየባቸው ቢሾፍቱ ፣ ቡራዩ ፣ ሰበታ ፣ ሻሸመኔ ፣ጅማ ፣ ወሊሶ፣ ጪሮና አሰላን ጨምሮ በሌሎች የክልሉ ከተሞችም ተግባራዊ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C