Jump to Navigation

Agency To Start Taking Finger Print For 20/80, 40/60 Condo Registrants

Published on: Mon, 2013-12-16 00:00
image of G+typology of condominium houses

የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖርያ ቤት ተመዝጋቢዎችን የጣት አሻራ ለመውሰድ የሚያስችለውን ስርዓት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው።

የአዲስ አበባ ቤቶች ማስተላለፍና አስተዳደር ኤጀንሲ አሻራ የመውሰድ ስራውን በ116 ወረዳዎች ለመጀመር ተገቢውን ዝግጅትና የሰው ሃይል ስልጠና በቅርቡ እንደሚጀመር አስታውቋል።

በታህሳስ ወርም ሙሉ በሙሉ የቅድመ ዝግጅቱ ስራ ተጠናቆ ወደ ምዝገባው ይገባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅትም ምዝገባውን ለማከናወን የሚረዱ ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ቤቶች ማስተላለፍና አስተዳደር ኤጀንሲው ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን መንግስቱ ተናግረዋል።

በቅድመ ዝግጅቱ ስራው የሚሳተፉት ባለ ድርሻ አካላት የአዲስ አበባ ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ይገኙበታል።

እስካሁን ድረስም የዝግጀት ሳራውን ሙሉ በሙሉ ተረክቦ እያከናወነው ያለው የኢንፎርሜሽን ደህንነት መረብ ኤጀንሲ  መሰረታዊ ናቸው  የተባሉ ቅድመ ዝግጅቶችን  አጠናቋል።

መረጃዎች እርስ በእርስ ለመናበብ የሚያስችል ሶፈት ዌር መዘጋጀቱን የሚናገሩት አቶ መስፍን፥ ይህንንም ከጣት አሻራ መውሰጃ ስካነርጋር በማያያዝ የሙከራ ስራውም ተጠናቋል ይላሉ።

ከዚህ ቀደም የነበረው የእጣ አወጣጥ ስርዓትን ለማከናወን መረጃ ይወሰድ የነበረው ከአንድ የመረጃ ቋት ብቻ የነበረ ሲሆን፥ ይህንን መረጃ ከተለያዩ ቦታዎች ተቀናጅቶ ለማግኘት የሚያስችልና የእጣ አወጣጡን ስርዓት ለማዘመን ስራም እየተከናወነ ይገኛል።

ይህ አሰራርም ቤት ኖሯቸው በድጋሚ ቤት ለማግኘት የተመዘገቡ ሰዎችን በመያዝ አግባብነት ያለው ፍትሃዊ የቤት ክፍፍል እንዲኖር ይረዳል ተብሏል።

Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C