Jump to Navigation

Administration To Undertake Redevelopment Programs In Four Sub Cities

Published on: Thu, 2014-01-16 00:00
Addis Ababa around kazanchis image

የአዲስ አበባ መሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ እስከ የካቲት መጨረሻ በ4 ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የግልና የመንግስት ቤቶችን አፍርሶ እንደገና ሊያለማ ነው።

የኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃረጎት አለሙ ፤ በተያዘው ዓመት በአራዳ፣ ቂርቆስ፣ ልደታ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ላይ 180 ሄክታር መሬት ለማልማት የዝግጅት ምዕራፍ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

መልሰው  ይለማሉ  ከተባሉ አከባቢዎች መካከልም ከዛንቺስ ኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል ፊት ለፊት፣ አፍሪካ  ህብረት እና  ዲ አፍሪክ አከባቢዎች  ይገኙበታል።

የልማት ተነሺዎቹ  የሚዘዋወሩባቸው የጋራ መኖሪያ እና የቀበሌ ቤቶችን  ሙሉ በሙሉ የማዘጋጀት ስራ እንደተጠናቀቀ  ቦታውን የማጽዳት ስራ ይጀመራል ብለዋል ስራ አስኪያጁ።

የከተማዋ ቤቶች ልማት አስተዳደር በበኩሉ ከ180 ሄክታር መሬት ለሚነሱ ነዋሪዎች 17 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ያዘጋጀ ሲሆን ተነሺዎችን የማዘዋወሩ እና ቦታውን የማጽዳቱ ስራ እስከ ሚያዚያ መጨረሻ እንደሚጠናቀቅ ተናግሯል።

ኤጀንሲው ከዚህ ጎን ለጎን ቀደም ሲል በባሻ ወልዴ ቁጥር አንድ እና ሁለት፣ በፓርላማ ማስፋፊያ፣ አሮጌ ቄራ፣ ልደታ እና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ከ30 ሄክታር በላይ ቦታዎች ላይ ያልፀዱትን ምቹ የማድረጉንም ስራ እያከናወነ ይገኛል።

Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C