Jump to Navigation

Administration To Construct 65 Thousand New Houses

Published on: Wed, 2013-12-25 00:00
Condominium House building image

በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የቤት እጥረት ለመፍታት  በተለያዩ አካባቢዎች  ግንባታቸው እይተከናወኑ የሚገኙት 95 ሺ ቤቶች ግንባታ መጠናቀቁን የከተማዋ ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከቀጣዩ ወር ጀመሮ ደግሞ  የ65 ሺየጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንደሚጀመር  ቢሮው ይፋ አድርጓል፡፡የቤቶቹ ግንባታም በየካ፣ በንፋስ ስልክና ቦሌ ክፍለ ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የቤቶቹን ግንባታ ለመጀመር 475 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል፤ለግንባታው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች፣ አስፈላጊው የሙያ ምዝና  የወሰዱ ተቋራጮችና አማካሪዎችን የመለየት ስራን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቀቸውን  የቢሮው ሃላፊ አቶ ጌታቸው ሃይለማርያም ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አሁን የተጠናቀቁትን ጨምሮ  2መቶ ሺ ገደማ ቤቶች ተገንብተዋል፡፡ ይሁንና ከአሁን በፊት በነበሩት የግንባታ ዓመታት  የውሃ፣ መብራት፣መንገድና ሌሎች የመሰረተ ልማት ተቋማት አቅርቦቶች ተቀናጅተው አለመስራት የግንባታ ሂደቱን ሲያስተጓጉሉት ቆይቷል፡፡

ከአሁን በኋላ በሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ  ላይ የመሰረተ ልማት አውታሮች ግንባታ ተጠናቀው ወደ ስራ እንደሚገባምነው  አቶ ጌታቸው የገለፁት፡፡

አቶጌታቸው  እንደሚሉት በጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ይስተዋል  የነበረውን የጥራት  ችግር ለመፍታት  በግንባታ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ባለሞያዎች  የብቃት ማረጋጋጫ ፈተና ይወስዳሉ፡፡

ምርመራ እና በግንባታ ግብዓቶች ፍተሻ  ላይ ከምን ግዜውም የበለጠ ጥንቃቄ እንደሚያደርግም ቢሮው አስታውቋል፡፡

አሁን ግንባታቸው የተጠናቀቁት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተቃሚዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Source: Ethiopian Radio and Television Agency (ERTA)Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C