Jump to Navigation

Adama-Wenji Road Construction To Commence

Published on: Tue, 2013-08-13 00:00
Image showing the current Wenji-Adama road

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 6 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዳማ ወንጂ መንገድ ሁሌም በአካባቢው ለሚመላሱ አሽከርካሪዎችም ሆነ መንገደኞች አመቺ አለመሆኑ ይነገራል፤ በተለይ ክረምት ሲመጣ ችግሩ ጎላ ይላል።

አስተያየት ሰጪዎቹ እንደሚሉት ይህንን መንገድ ለማሰራት ከባድ አይደለም ፥ ምክንያቱም ችግር ያለበት የመንገድ ክፍል እርዝማኔ ከ10 ኪሎ ሜትር የማይበለጥ በመሆኑ ነው ።

የወንጂ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ ዘይነባ አማን እንደሚሉትም ፥  የዚህ መንገድ አለመሰራት ከተማዋን ያገለላት ሲሆን ፥ በእድገቷ ላይም የራሱን ተጽእኖ እያሳረፈ  ነው ።

የአዳማ ከተማ ከንቲባና የጥቃቅንና አነስተኛ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አህመድ የሱፍ በበኩላቸው ፥ መንገዱ ካለው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንጻር የአዳማ አስተዳደር በ2006 ዓ.ም መንገዱን ለመገንባት የሚያስችል ውሳኔ አሳልፏል፤ በአሁኑ ጊዜም የዲዛይን ስራው ተጠናቋል ብለዋል።

የግንባታውን ወጪ አስተዳደሩ ይሸፍናል ያሉት ከንቲባው ፥ በአካባቢው ያሉት ባለሀብቶችም የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ፍላጎታቸውን እየገለጹ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ከአዳማ ወንጂ ለሚደርሰው ለዚህ መንገድ ግንባታ ከሁለት አመት በፊት አዳማ በሚገኘው አባገዳ የሰብሰባ አደራሽ በተከናወነው የገቢ ማሳባሰቢያ ዝግጅት እስከ 10 ሚሊዮን ብር ቃል ተገብቶ ነበር ያሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ፤ ይሁንና ይህን ሲሰሩ የነበሩት ኮሚቴዎች ድምጻቸው ጠፍቷል ፤ የተሰባሰበው ገንዘብም የት እንደደረሰ እንደማያውቁም ነው የሚናገሩት።

ይህን በተመለከተ ገንዘቡ በተለዩ ባንኮች በዝግ አካውንት መቀመጡንና የተወሰነው ደግሞ በሰዎች እጅ እንደሚገኝ ፤ የመንገዱ ግንባታ እየተካሄደም ጉዳዩ እንዲጣራ ከሚመለከታቸው ጋር እንሰራለን ብለዋል አቶ አህመደ የሱፍ ።

ጉዳዩን በተመለከተ በወቅቱ ገንዘቡን ሲያሰባሰቡ ነበሩ የተባሉት የኮሚቴው ሰብሰባቢ እና አባልን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ግለሰቡ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አልተሳካም።

የኦሮሚያ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በበኩሉ ፥ ለመንገዱ ግንባታ ተሰባስቧል የተባለው ገንዘብ የህዝብ ሀብት እንደሆነ በመግለፅ ጉዳዩን በዝምታ እንደማያልፈው አስታውቋል።

በመሆኑም ጉዳዩን የማጣራትና የመከታተል ስራው እንደሚካሄድ ነው የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጠይብ አባፎጊ የተናገሩት ።

Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C