5th Cities Week Marks In Bahir Dar
አምስተኛው ሃገር አቀፍ የከተሞች ሳምንት ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት በባህር ዳር ከተማ ይከበራል።
ሳምንቱ ከተሞቻችን የተመቻቸ የኢንተርፕራይዞች ልማት ማዕከል በመሆን የመለስን ውርስ ያስቀጥላሉ በሚል መሪ ቃል ይከበራል።
198 ከተሞች ምርጥ ተሞክሮዎቻቸውን በማስተዋወቅና ልምድ በመቅሰም ለተሻለ ስራ መነሻ የሚያገኙበት አጋጣሚንም ይፈጥራል ተብሏል።
ከተሞች በስራ እድል ፈጠራና በኢንቨስትመንት የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ከእነመፍትሄው የሚጠቁሙ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)
- 1663 reads