Jump to Navigation

50 Thousand Condos To Be Transferred To Beneficiaries

Published on: Thu, 2014-01-23 00:00
Condos in Addis Ababa image

በአዲስ አበባ ለነባር የ20/80 ቤቶች ፕሮግራም ተመዘጋቢዎች ተገንብተው የተጠናቀቁ 50 ሺ ቤቶች ሊተላለፉ ነው።

የ10/90 ቤት ፈላጊ ተመዝጋቢዎች ሙሉ በሙሉ በዚህ ዓመት መጨረሻ ቤታቸውን እንደሚረከቡም የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታውቋል ፡፡

በመዲናዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማሟላት የከተማ አስተዳደሩ ነባርና አዳዲስ የቤት ፕሮግራሞችን ይፋ አድርጎ በድጋሚ ምዝገባ ካካሄደ ስድስት ወራት አልፏል፡፡

ቁጠባን መሰረት ባደረጉ በሁሉም የቤቶች ፕሮግራም 900 ሺህ የሚደርስ የከተማዋ ነዋሪዎች ተመዝግበዋል፡፡

ነዋሪዎቹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክም የሚጠበቅባቸውን ገንዘብ እየቆጠቡ ነው፡፡

ከቁጠባው ጎን ለጎንም የከተማ አስተዳደሩ ቤቶችንም እየገነባ ሲሆን ፥ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ በአሁኑ ወቅት የ75 ሺህ ቤቶች ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው ብለዋል፡፡

የተጠናቀቁ ቤቶችን ለማስተላለፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቋልም ብለዋል ዋና ስራ አስኪያጁ፡፡

መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የከተማዋን ነዋሪዎች ፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የቤት ባለቤት በሚያደርገው የ40/60 ፕሮግራም ከ160 ሺ በላይ ዜጎች ተመዝግበዋል፡፡

የእነዚህ ቤቶች ግንባታም በአምስት የግንባታ ቦታዎች እንደተጀመሩ የአዲስ አበባ የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዮሀንስ አባይነህ አስታውቀዋል፡፡

ለ40/60 የቤቶች ፕሮግራም ቀጣይ 12 ሺህ ቤቶች ለመገንባትም የመሬት መረጣና ሌሎች አስፈላጊ ስራዎች ተጠናቀው ወደ ግንባታ ለመግባት ዝግጅት መጠናቀቁን እንደተገለፀ የዘገበው ኢሬቴድ ነው።

Source: Fana Broadcasting Corporate (FBC)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C