A 2.5 Billion Birr Power Transmission Line Factory Being Built In Sebeta
በ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በሰበታ የሀይል ማስተላለፊያ ገመድ ፋብሪካ እየተገነባ ነው
የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በሀገራችን የሚመረተው የሀይል ማስተላለፊያ ገመድ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የሀገሪቱን ፍላጎት ማሟላት ደረጃ ላይ ይደርሳል አለ ።
ኢንስቲትዩቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው 2007 ላይ ሀገሪቱ የሚያስፈልጋት የሀይል ማስተላለፊያ ገመድ መጠን ከ250 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ይሆናል ።ይህን ፍላጎት አሁን በአገሪቱ ያሉት ጥቂት ፋብሪካዎች እንደማያሟሉ ነው ያመለከተው ።በመሆኑም ፍላጎትና አቀርቦቱን ለማሟላት እንዲቻል ኢንስቲትዩቱ ሳይገን ቢ ኤም ከተባለ የቱርክ ኩባንያ ጋር የፕሮጀክት ውል በመግባት የሀይል ማስተላለፊያ ገመድ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ እንዲጀመር አስችሏል ።
ኩባንያው በአሁኑ ወቅት በሰበታ በወሰደው አስራ አምስት ሄክታር መሬት ላይ በ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ የፋብሪካውን ግንባታ እያካሄደ ይገኛል ።
አስፈላጊ የሆኑ የማሽነሪ እቃዎችን በማሟላት ላይም ሲሆን ፥ የድርጅቱ ስራ ተጠናቆ በሚቀጥለው አመት ታህሳስ ወር ላይ ምርት እንደሚጀምርም ነው የተመለከተው ።
ባልደረባችን ካሳዬ ወልዴ እንደዘገበው ፋብሪካው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጀምሮ ለቤት ውስጥ ፍጆታ የሚያገለግሉ ገመዶችንም ያመርታል።
Source:-Fana broadcasting corporat
- 686 reads