Jump to Navigation

Ministry, Chinese Firm sign Agreement To Construct Industry Zone Near Dire Dawa Town

Published on: Sun, 2013-09-01 16:11
Image of the town of Dire Dawa

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በድሬዳዋ አቅራቢያ የሚገነባውን የኢኮኖሚ ዞን ወደ ተግባረ የሚያሸጋግር ስምምነት ከአንድ የቻይና ኩባንያ ጋር ተፈራረመ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሰሞኑን ከቻይናው የኢንዱስትሪ ዞኖች ልማት ማህበር ጋር በቤጂንግ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ኩባንያው በድሬዳዋ አከባቢ ላይ ለሚገነባው የኢስዱስትሪ የኢኮኖሚ ዞን ማስተር ፕላን ያስገኛል፣የኢኮ ጥናትና የስፔሻል ፕላኑን ያጠናቅራል፣ከዚህም በተጨማሪ በግንባታ ሂደትና ከግንባታ በኋላ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ይሰራል ተብሏል፡፡
በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ስዩም መስፍን ሀገራችን ወደ ኢንዱስትሪ መር የልማት ስትራቴጂ ለመሸጋገር የምታደርገው ጥረት እውን ለማድረግ የተፈረመው ስምምነት መሰረት የሚጥል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ኩባንያው በረዥም ጊዜ ጥናትና የማግባባት ስራ የተገኘ መሆኑን ያብራሩት አምባሳደር ስዩም መስፍን በሀገራችን ለታሰበው የኢንዱስትሪ ልማት የረዥም ጊዜ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሲሳይ ገመቹ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የሚገነቡት የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ ዞኖች የግብርና ልማትን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ገልፀው ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ስምምነቱ በመፈረሙ ብቻ የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ፍላጎትና ትኩረት እንደሚኖራቸው የጠቆሙት አቶ ሲሳይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ግንባታ ለመግባት ጥረት እንደሚደርግ አስታውቀዋል፡፡
የኩባንያው ፕሬዚዳንት ሚስተር ሺን ዥዋን በፊርማ ስነ ስርአቱ ላይ እንዳሉት በአፍሪካ ስትራቴጂካዊ ቦታ ያላት ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ለኢንዱስትሪ ልማት የሰጠችው ትኩረት የሚደነቅ ነው፡፡
ቻይናም ሆነች ኩባንያቸው ይህንን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት ለማሳካት የተቻላቸውን ሁሉ በማድረግ ምን ጊዜም ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል፡፡
Source: Ethiopian Radio and Television Agency (ERTA)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C