Jump to Navigation

Endeselassie Dedebit-Dashen Road To Complete in 2006 E.C

Published on: Sat, 2013-08-03 15:37
Image of Endeselassie Dedebit-Dashen concrete asphalt road

ከ 1ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኝው የእንደ ስላሴደደቢት-ዳሽን የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ በሚቀጥለው አመት ይጠናቀቃል።

ከ12 በላይ ከተሞችን አቋርጦ በማለፍ ተጠቃሚ የሚያድርገው እና 80 በመቶ ስራውየተጠናቀቀው ይህ 244 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀት ስራውየተጀመረው ከሁለት አመት በፊት ሲሆን በእቅዱ መሰረት እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያመንገዶች ባለስልጣን አመልክቷል።

ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከሽሬ ወደ ዳሽን ለመድረስ በጎንደር አሊያም በሁመራ በመዞርከ10 ሰዓት በላይ ይፈጅ የነበረውን ጉዞ በአማካይ ወደ 4 ሰዓት ዝቅ ያደርገዋል እንደ ፋና ዘገባ ።

በተጨማሪም በአካባቢው እየተገነባ ያለውን ግዙፍ የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ስራናየትራንስፖርት ፍሰትን በማቀላጠፍ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በመደገፍ ከፍተኛ ድርሻእንደሚያበረክት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አመልክቷል።

Source: Ethiopian Radio and Television Agency (ERTA)



Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C