Jump to Navigation

Case

Case's related to construction.

A case involves a Real-estate construction company (ካንትሪ ክለብ ዴቨሎፐር የረር ቪው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት) on labor issue

Published on: Mon, 2013-12-16 14:33

ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ሲሆን በፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የቀረበው በአሁኑ ተጠሪዎች
ከሣሽነት ነው፡፡ ቀርቦ የነበረው ክስ በተከሣሽ ድርጅት ውስጥ በአናጢነት ሙያ ተቀጥረን 1ኛ ከሣሽ በቀን ብር 36 ፣ 2ኛ ከሣሽ ብር 39 እና 3 ከሣሽ ብር 20 እየተከፈለ በመስራት ላይ እያለን ነሀሴ 17 ቀን 2002 ዓ.ም ያለአግባብ ከስራ ላይ ያሰናበተን ስለሆነ ወደ ምድብ ስራችን እንድንመለስ ወደ ስራ የማይመልሰን ከሆነ ደግሞ በህጉ መሠረት ሊከፍለን የሚገባውን ክፍያዎች እንዲከፍለን የሚል ነው፡፡ ተከሣሽ .......

please go to the pdf. to see the case

A case involves a large-scale construction company (ድራጋዶስ ኮንስትራክሽን) on extra-contractual liablity Law issue

Published on: Mon, 2013-12-16 14:26

ጉዳዩ ከውል ውጪ ኃላፊነትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን መሠረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ ጥቅምት 22 ቀን 1998 ዓ.ም. በመሠረተው ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱ ይዘትም፡- ተጠሪ በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ አካባቢ የመንገድ ሥራ ሲያከናውን በአመልካች ንብረት ላይ ግምቱ ብር 25,569.85 /ሃያ አምስት ሺህ አምስት መቶ ስልሣ ዘጠኝ ብር ከሰማኒያ አምስት ሳንቲም/ የሆነ ጉዳት ማድረሱን ገልፆ ይህንኑ ገንዘብ ከነወለዱ ወጪው ጋር እንዲተካ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው፡የአሁኑ ተጠሪም.............

for further reading refer to the case please.

A case involving large-scale construction company (ሰንሻይን ኮንስትራክሽን) on labor issue

Published on: Mon, 2013-12-16 14:18

ጉዳዩ የተጀመረው በፌደራል የመ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የታች ተከሣሽ ሲሆን የአሁን መ/ሰጭ የታች ከሣሾች ነበሩ፡፡ መ/ሰጭ በታች ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በመቀጠር በአናፂነት ሙያ ሲያገለግሉ ቆይተው ሌላ ሣይት (ቦታ) ሥራ እያለው ሥራው አልቋል በማለት ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሥራ ውላችንን አቋርጦብናል ስለዚህ የአገልግልት ክፍያ የማስጠንቀቂያ የሁለት ወር የዘገየበት የስንብት የስድስት (6) ወር ክፍያ እና የትርፍ ሰአት ክፍያ እንዲወሰንልን በማለት........

Refer the full part; to the case please.

A case involving a large-scale construction company (ፍሊንትሰቶን ኢንጂነሪንግ) on Gift contract law issue

Published on: Mon, 2013-12-16 11:37

ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ በዚሁ ፍ/ቤት ተጠሪዎች ከሳሾች የነበሩ ሲሆን አመልካች ሁለተኛ ተከሣሽ ነበረ፡፡ ተጠሪዎቹ ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ክስ አንደኛ ተከሣሽ ወ/ሮ ወርቅይጠሩ ሰርፀመዴኀን ከመሞታቸው በፊት ለክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት በስጦታ ስለሰጡኝ ይጽደቅልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ የተጠሪዎች አባት ተቃውመው የስጦታ ውል በፍ/ቤቱ ፈራሽ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ነገር ግን.......

please go to the pdf. to see the case

A case involves a contractor (ብሄራዊ መሃንዲሶች ስራ ተቋራጭ ድርጅት) on labor law issue

Published on: Mon, 2013-12-16 11:29

ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡........

please refer below to see the case

(case) large scale construction company (ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግል ማህበር) on labour issue

Published on: Mon, 2013-12-16 10:46

ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዳይ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሠረት የሚታይ የአሠሪና ሠራተኛ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ በፌደራሌ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ ነው፡፡ በአመልካች ላይ ክስ የመሠረተውም የስራ ውላ ከሕግ ውጪ ተቋርጦብኛል፤ ስለዚህ ውዝፍ ደመወዜ ተከፍሎኝ እና ያልተሰጠኝ የአመት ፈቃድ ተሰጥቶኝ ወደ ስራዬ እመለስ ዘንድ ይወሰንልኝ በማለት ነው፡፡አመልካች.......

Go to the pdf. please to see the full part of the case

A case involves large scale construction company (ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኃላ.የተ.የግል ማህበር) on labor law issue

Published on: Sat, 2013-12-14 12:08

ጉዳዩ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅን መሠረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ መጋቢት 18 ቀን 2000  በተፃፈ ክስ በአመልካች ድርጅት በሹፌርነት ተቀጥረው እየሠሩ ባለበት ሁኔታ ያለአግባብ ከስራ መሰናበታቸውን ገልፀው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎአቸው ወደ ስራ እንዲመለሱ ወይም የካሣ፣ የስራ ስንብት፣ የ65 ሣአት ትርፍ ሣአት፣ የ16 ቀን የእረፍት ቀን፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜና ክፍያ የዘገየበት ክፍያ ተከፍሎአቸው ከስራ እንዲሰናበቱ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት ጠይቀው........

to read more , Go to the pdf. please.

A case involves large scale construction company (ሳሊኒ ኮንስትራክሽን) on labor law issue

Published on: Sat, 2013-12-14 12:01

ይህ የሰበር ጉዳይ በግራ ቀኙ መካከል የተነሣውን የአሠሪና ሠራተኛ ክርክር ተቀብሎ በማስተናገድ የሥ-ነገር ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት የትኛው ነው? የሚለውን አስመልክቶ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዳኝነት መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ለመለየት ሲባል የቀረበ ነው፡፡ የአሁን አመልካች አሠሪዬ የአሁን ተጠሪ ያለአግባብ ከሥራ ያሰናበተኝ ስለሆነ ወደ ሥራ
ይመልሰኝ ይህ ካልሆነ ያለአግባብ በመሰናበቴ ምክንያት ልዩ ልዩ ክፍያዎችን ይፈፅምልኝ በማለት ባቀረቡት ክስ በማስረጃነት የቀረቡት ግራ ቀኙ ያደረጉትን የሥራ ቅጥር ውል ነው፡፡

for the full part ,Go to the case please.

(case) Investment construction (ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ) on contract issue

Published on: Sat, 2013-12-14 11:51

ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በከፋዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁኑ ተጠሪ ለፍ/ቤቱ ባቀረበው ክስ አመልካች ዘመናዊ ሆስፒታል ለመገንባት ቦታ ጠይቀው 1,931 ካ.ሜ ቦታው ተሰጥቷቸው ግንባታውን ስላቋረጡ ውለ ተሰርዞ ግንባታው በራሳቸው ወጪ አፌርሰው ቦታውን ለተጠሪ እንዲያስረክቡ እንዲሁም ከ1996 ዓ.ም - 1999 ዓ.ም የቦታና የቤት ግብር ብር 52,782.35(ሃምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ሺህ ብር ከሰልሳ አምስት ሳንቲም) እንዱከፍለ በማለት.................

for further reading refer to the case please.

(case) Home Construction S.C( የምጥን መንደር መኖሪያ ቤቶች የህብረት ሥራ ማህበር) on property right

Published on: Sat, 2013-12-14 11:39

ጉዳዩ በሁከት ይወገድ ክስ መነሻነት ክርክር ተካሂዶ የተሰጠውን ውሳኔ መሠረት በማድረግ የተጀመረውን የአፈጻጸም ክርክር የሚመለከት ነው፡፡ ከመዝገቡ እንደሚታየው የአሁኑ አመልካች የሁከት ይወገድልኝ ክስ በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ መስርቶ ክርክር ከተደረገ በኋላ፣ የፍርድ
ባለመብት ሆኖአል፡፡.........

read more the case please.

Pages

Subscribe to RSS - Case


Main menu 2

Lambadi Software Developer P.L.C